Popular Posts

Wednesday, July 27, 2011

ማን እንደኔ

ማን እንደኔ ይሆናል?
ማንስ እኔን ይመስላል?
ከ አላዛር እበልጣለሁ
ከ ኢየሱስም እልቃለሁ
በየጊዜው እየሞትኩኝ
በየጊዜው እነሳለሁ::
//-//
(To "the old self, the old man" which dies and rises now and then!

To us who fall and rise every time)__sorry for the GURAMAYLE!
ሐምሌ 18 2003 ዓ.ም
4:45 ከ ምሽቱ
አፍንጮ በር
ሃሳቡ ቀደም ብሎ ቀን ላይ ተፀንሶ ነበር

Monday, July 25, 2011

ኦ ማንዴላ

ኦ ማንዴላ
የማትሰክር በጠላ
በአረቄ የማትጠነብዝ
በወይን የማትደነዝዝ::
ያን ሁሉ ስቃይ ተግተህ
ያን ሁሉ ግፍ ጠጥተህ
ሰክረህ ያልተንገዳገድከው
ይኸ ድንቅ አምላካችን
ምን ማርከሻ ቢሰጥህ ነው??

ኦ ማንዴላ
የማትሰክር በጠላ
በአረቄ የማትጠነብዝ
በወይን የማትደነዝዝ
ያን ሁሉ ዝና ጨልጠህ
ያን ሁሉ ክብር አንዶቅዱቀህ
በስልጣን አረቄዋ
በናላ አዟሪዋ እጅ ወድቀህ
ሰካራም ሆነህ ያልቀረኸው
ይኸ ግሩም ጌታችን
ምን ማርከሻ ቢሰጥህ ነው??
//-///
ሐምሌ 17 2003 &ወደ ምሽት( ነገ የ ማንዴላ 93ኛ ዓመት የልደት በዓል ይከበራል)
ፒያሳ& ኪያብ ካፌ
ከወዳጄ በረከት ጋር ስለ ማንዴላ አውርተን ውስጤ ቢነሳሳ ጊዜ ጻፍኩት
ለማንዴሎች ሁሉ ጌታ ለጌታ ኢየሱስ!!

Saturday, July 23, 2011

ነገረ-ቆብ

እውቀትን መረመርናት

ውስጠ ሚስጥሯን በልትናት

እንኳን ደስ ያለን ያሉ

የራስ ቆብ ይደፋሉ::

ደግሞ

አለምን ብንመርምር

ደስታን ከሀዘን ብንደምር

"ችቦ አይሞላም ወገቧ"

ከንቱነት ነው ቀለቧ

ትቅርብን እንፍታት ያሉ

የራስ ቆብ ይደፋሉ::

//---///

ሓምሌ 16 2003 ዓ.ም

7:58 ከሰዓት

እንቁላል ፋብሪካ

ለወዳጄ ለ ኢየሩሳሌም አሰግድ ምርቃት ግብጃ ሄጄ የጫርኩት

Saturday, July 16, 2011

ዱቤ 1

እግዚአብሄር ዱቤ ይወዳል
ፀሎት በዱቤ ይወስዳል
ግን አይደለም እንደ ሰው
በጊዜው በሰአቱ
ጨምሮ ነው ሚመልሰው::

ሓምሌ 5 2003 ከሰዓት
አፍንጮ በር አዲስ አበባ
በስራ ተወጥሬ መጣብኝ

Saturday, July 9, 2011

ሀገሬ በሰማይ?

"ሀገሬ በሰማይ ነው" ብዬ ፎክሬ ዝቼ
"ሀገሬን ከነጣጣዋ" "ለምድራውያኑ" ትቼ
ወደ ሰማያ ተነጥቄ ደጆቿን ብነካካ
"ወደ ምድር ሂድ" ተባልኩ
የአንድዬ አላማ
"ግዛት ማስፋት" ነው ለካ!

ሀምሌ 1 2003 ዓ.ም
6 ኪሎ ድህረ ምረቃ በተ-መጻህፍት

Tuesday, July 5, 2011

ፀሎተ ዘወትር


ፀሎተ ዘወትር

ስንት መንግስት ሰማን ስንት መንግስት አዬን
ስንት መንግስት አጠገበን ስንት መንግስት አሰቃዬን::
እባክህ
"መንግስተ-ምድር" ይወረድ "መንግስተ ምድር ይውጣ"
ፍቃድህ በምድር ትሁን መንግስትህ በምድር ትምጣ::

20-10-2003 .
. ቤላ ::ከጣልያን ኤምበሲ አጥር ስር
                                                                                        ጠዋት 2:30