Popular Posts

Monday, July 25, 2011

ኦ ማንዴላ

ኦ ማንዴላ
የማትሰክር በጠላ
በአረቄ የማትጠነብዝ
በወይን የማትደነዝዝ::
ያን ሁሉ ስቃይ ተግተህ
ያን ሁሉ ግፍ ጠጥተህ
ሰክረህ ያልተንገዳገድከው
ይኸ ድንቅ አምላካችን
ምን ማርከሻ ቢሰጥህ ነው??

ኦ ማንዴላ
የማትሰክር በጠላ
በአረቄ የማትጠነብዝ
በወይን የማትደነዝዝ
ያን ሁሉ ዝና ጨልጠህ
ያን ሁሉ ክብር አንዶቅዱቀህ
በስልጣን አረቄዋ
በናላ አዟሪዋ እጅ ወድቀህ
ሰካራም ሆነህ ያልቀረኸው
ይኸ ግሩም ጌታችን
ምን ማርከሻ ቢሰጥህ ነው??
//-///
ሐምሌ 17 2003 &ወደ ምሽት( ነገ የ ማንዴላ 93ኛ ዓመት የልደት በዓል ይከበራል)
ፒያሳ& ኪያብ ካፌ
ከወዳጄ በረከት ጋር ስለ ማንዴላ አውርተን ውስጤ ቢነሳሳ ጊዜ ጻፍኩት
ለማንዴሎች ሁሉ ጌታ ለጌታ ኢየሱስ!!

2 comments:

  1. ወዳጄ ፀግሽ ግሩም ዕይታ……ታዲያ ይህንን ማርከሻ ለእኛዎቹስ 'ጀባ' ቢልልን እንዴት ደግ ነበር !
    አበርክትኦቱን ወድጄዋለሁ!!!

    ReplyDelete
  2. ውድ በፀጋ የዳንከው(ይህንን ማወቅ ምንኛ ጥበብ ነው!) አመሰግናለሁ::
    አሜን ከማርከሻው ትንሽ ጠብታ ለኛዎቹ ያድልልን:: እኛም ብዙ አይነት ስካር አለብንና ማርከሻውን ይስጠን

    ReplyDelete