ኦ ማንዴላ
የማትሰክር በጠላ
በአረቄ የማትጠነብዝ
በወይን የማትደነዝዝ::
ያን ሁሉ ስቃይ ተግተህ
ያን ሁሉ ግፍ ጠጥተህ
ሰክረህ ያልተንገዳገድከው
ይኸ ድንቅ አምላካችን
ምን ማርከሻ ቢሰጥህ ነው??
ኦ ማንዴላ
የማትሰክር በጠላ
በአረቄ የማትጠነብዝ
በወይን የማትደነዝዝ
ያን ሁሉ ዝና ጨልጠህ
ያን ሁሉ ክብር አንዶቅዱቀህ
በስልጣን አረቄዋ
በናላ አዟሪዋ እጅ ወድቀህ
ሰካራም ሆነህ ያልቀረኸው
ይኸ ግሩም ጌታችን
ምን ማርከሻ ቢሰጥህ ነው??
//-///
ሐምሌ 17 2003 &ወደ ምሽት( ነገ የ ማንዴላ 93ኛ ዓመት የልደት በዓል ይከበራል)
ፒያሳ& ኪያብ ካፌ
ከወዳጄ በረከት ጋር ስለ ማንዴላ አውርተን ውስጤ ቢነሳሳ ጊዜ ጻፍኩት
ለማንዴሎች ሁሉ ጌታ ለጌታ ኢየሱስ!!
ወዳጄ ፀግሽ ግሩም ዕይታ……ታዲያ ይህንን ማርከሻ ለእኛዎቹስ 'ጀባ' ቢልልን እንዴት ደግ ነበር !
ReplyDeleteአበርክትኦቱን ወድጄዋለሁ!!!
ውድ በፀጋ የዳንከው(ይህንን ማወቅ ምንኛ ጥበብ ነው!) አመሰግናለሁ::
ReplyDeleteአሜን ከማርከሻው ትንሽ ጠብታ ለኛዎቹ ያድልልን:: እኛም ብዙ አይነት ስካር አለብንና ማርከሻውን ይስጠን